ቀጥታ፡

አቶ ተመስገን ጥሩነህ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2016(ኢዜአ)፦ አቶ ተመስገን ጥሩነህ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ፡፡

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን በ15ኛ መደበኛ ስብሰባው የአቶ ተመስገን ጥሩነህን የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነት ሹመት አጽድቋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአቶ ተመስገንን የሥራ ልምድ ዘርዝረው ለምክር ቤቱ ባቀረቡት መሰረት ምክር ቤቱ በሙሉ ድምጽ ሹመቱን ማጽደቁን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም