ቀጥታ፡

የኢትዮ-ጅቡቲን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የሚያሳይ የፎቶ አውደ-ርዕይ በጅቡቲ ተከፈተ

አዲስ አበባ፤ ጥር 29/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያና የጅቡቲን የ127 ዓመታት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የሚያስቃኝ የፎቶ አውደ-ርዕይ በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተከፍቷል።

በአውደ ርዕዩ መክፈቻ ላይ በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሀኑ ጸጋዬ እንደተናሩት አውደ-ርዕዩ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ጠንካራ ግንኙነት የሚያጎለብት ነው ብለዋል።

በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር ፍሰሀ ሻወል በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ታሪካዊ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር አውደ ርዕዩ ሚና ይኖረዋል ነው ያሉት።


 

የጅቡቲ የግብርናና ውሃ ሚኒስትር ሙሀመድ አህመድ አዋሌህ በኢትዮጵያና በጅቡቲ መካከል ያለውን ጠንካራ ግንኙነት ማድነቃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ ቀጣናዊ ትስስርን ለማጠናከር በመሰረተ ልማት፣ በታዳሽ ሀይል፣ በንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፎች በትብብር እየሰሩ መሆናቸውንም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም