ቀጥታ፡

በጀኔራል አበባው ታደሠ የተመራውና በዓለም አቀፍ የመከላከያ ትዕይንት ላይ ተሳታፊ የነበረው ልዑክ ቆይታውን አጠናቆ ተመለሰ

አዲስ አበባ፤ ጥር 28/2016 (ኢዜአ)፦ በጦር ሀይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀኔራል አበባው ታደሠ የተመራውና በሳዑዲ ዓረቢያ ተዘጋጅቶ ለእይታ በቀረበው ዓለም አቀፍ የመከላከያ ትዕይንት(WDS) ተሳታፊ የነበረው ልዑክ ቆይታውን አጠናቆ ተመልሷል።

በሳዑዲ ዓረቢያ መከላከያ ሚኒስቴር የወታደራዊ አታሼ አስተዳደር አስተባባሪነት እ.አ.አ በ04/02/2024 ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ105 በላይ ለሚሆኑ ሀገራት ልዑካን እና ለጎብኝዎች ክፍት ሆኖ የቆየው አለም አቀፍ የመከላከያ ትዕይንት ተጠናቋል።

የዝግጅቱን በይፋ መከፈት ተከትሎ በጦር ሃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ መክፈቻዉን ጨምሮ ትዕይንቱን በመታደም ቆይታውን አጠናቆ ተመልሷል።

ጄኔራል አበባው ታደሠ እና ልዑካቸው በሳዑዲ ዓረቢያ ቆይታቸው የሳዑዲ የካዴት ትምህርት ቤትን፣ የወታደራዊ አልባሳት አምራች ኩባንያን፣ የኢንዱስትሪ የምርምር ማዕከላትን መመልከታቸውም ከመከላከያ ሰራዊት የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም