የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በነገው ዕለት 14ኛ መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል - ኢዜአ አማርኛ
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በነገው ዕለት 14ኛ መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል
አዲስ አበባ፤ ጥር 27/2016(ኢዜአ)፦ የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በነገው ዕለት 14ኛ መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በምክር ቤት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 14ኛ መደበኛ ስብሰባ በነገው ዕለት ጥር 28/2016 ዓ.ም ያካሂዳል።
በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 55 (17) በተቀመጠውና በምክር ቤቱ የአሠራርና የአባላት ስነምግባር ደንብ ቁጥር 6/2008 መሠረት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በምክር ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች የሚሰጡትን መልስና ማብራሪያ እንደሚያዳምጥም ተመላክቷል።