ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ቡድን የደቡብ አፍሪካ አቻውን አሸነፈ

አዲስ አበባ፤ ጥር 26/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የደቡብ አፍሪካ አቻውን 3ለ0 በሆነ ውጤት አሸነፈ።

ከ17 ዓመት በታች ሴቶች የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ሁለተኛ ዙር የመጀመሪያ ጨዋታ የኢትዮጵያና ደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ ቡድኖች ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም አካሂደዋል።


 

ጨዋታውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን 3ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

ግቦቹን ማንአዩሽ ተስፋዬ በ10ኛው ደቂቃ የመጀመሪያዋን ጎል ስታስቆጥር፣ ህዳአት ካሡ ሁለት ጎሎችን በ19ኛውና በ72ኛው ደቂቃ አስቆጥራለች።

የብሔራዊ ቡድኖች ቀጣይ ጨዋታ በደቡብ አፍሪካ እንደሚካሄድ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም