ቀጥታ፡

53ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ፍፃሜውን ያገኛል

አዲስ አበባ፤ ጥር 26/2016(ኢዜአ)፦ ከጥር 21 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ስድስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው 53ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ፍፃሜውን ያገኛል፡፡

የአትሌቲክስ ሻምፒዮናው የስድስተኛ እና የመጨረሻው ቀን ውድድር እየተካሄደ ነው።


 

በሻምፒዮናው በካሜሮን በሚካሄደው 23ኛው የአትሌቲክስ ሻምፒዮና እና በጋና አክራ በሚካሄደው የመላው አፍሪካ ውድድር እንዲሁም በፓሪስ ኦሎምፒክ የሚሳተፉ አትሌቶች ተለይተውበታል፡፡

በማጠናቀቂያ ፕሮግራሙ የሴቶች የምርኩዝ ዝላይ እና የሴቶች እና የወንዶች የ1 ሺህ 500 ሜትር ውድድሮች እየተካሄዱ መሆናቸውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም