የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቶሮንቶ የሚያደርገውን ሳምንታዊ በረራ ሊያሳድግ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቶሮንቶ የሚያደርገውን ሳምንታዊ በረራ ሊያሳድግ ነው
አዲስ አበባ፤ ጥር 25/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ካናዳ ዋና ከተማ ቶሮንቶ የሚያደርገውን ሳምንታዊ በረራ ወደ ሰባት ሊያሳድግ መሆኑን አስታውቋል።
አየር መንገዱ የሳምንታዊ በረራ ማሻሻያውን ከመጋቢት 23/2016 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚጀምርም ገልጿል
የካናዳ የንግድ፣ የቴክኖሎጂ እና የባህል ማዕከል ወደሆነችው ቶሮንቶ ከተማ የሚያደርገውን አምስት ሳምንታዊ በረራ ከፍ በማድረግ በሰባቱም የሳምንቱ ቀናት በረራ ማድረግ እንደሚጀምር ነው አየር መንገዱ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መረጃ ያስታወቀው።