የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ እጩ መኮንኖችን እያስመረቀ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ እጩ መኮንኖችን እያስመረቀ ነው
አዲስ አበባ፤ ጥር 25/2016 (ኢዜአ)፦ በሁርሶ ኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ማዕከል የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ ለ24ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን የአንድነት ኮርስ እጩ መኮንኖችን በዛሬው እለት እያስመረቀ ይገኛል።
በምረቃ ሥነ-ስርዓቱ የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር የተለያዩ ሀገራት ወታደራዊ አታሼዎች ጀኔራል መኮንኖችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ተመራቂዎች በእውቀት፣ በክህሎት እና በአስተሳሰብ ሙሉ የሚያደርጋቸውን የመሪነት ስልጠና የወሰዱ ሲሆን ከተመራቂዎች መካከል ሴቶች እንደሚገኙበትም ታውቋል ያመለክታል።