የምግብ ስርዓት ትራንስፎርሜሽን ፍኖተ ካርታ ላይ ትኩረት ያደረገ አውደ ጥናት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የምግብ ስርዓት ትራንስፎርሜሽን ፍኖተ ካርታ ላይ ትኩረት ያደረገ አውደ ጥናት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፤ ጥር 22/2016(ኢዜአ)፦ የምግብ ስርዓት ትራንስፎርሜሽን ፍኖተ ካርታ ላይ ትኩረት ያደረገ አውደ ጥናት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው
ፍኖተ ካርታው ግብርና ሚኒስቴርና የጤና ሚኒስቴርን ጨምሮ የተለያዩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችና ባለ ድርሻ አካላት ባካተተ መልኩ ተዘጋጅቷል።
ፍኖተ ካርታው ምርታማነትን መጨመር፣ የገጠር ኑሮ ማሻሻል፣ ግብርናን ከሌሎች ኢንዱስትሪዎች ጋር ማቀናጀት፣ አካበቢ ጥበቃን ማጠናከርና ከምግብ ጋር የተያያዙ የጤና ችግሮችን መግታት ከያዛቸው ጉዳዮች መካከል ነው ።
እነዚህን ግቦች ለማሳካት ደህንነቱ የተጠበቀና በንጥረ ነገር የበለጸገ ምግብን ተደራሽ ማድረግ፣ የግብርና ሜካናይዜሽን ማስፋፋት፡ የምግብ ስርአትን ለማሻሻል የሚረዱ ቴክሎጂዎችና ፈጠራዎች እየተተገበሩ ካሉ ተግባራት መካከል ናቸው።
ፍኖተ ካርታው ያለበት ደረጃ፣ የተገኙ ውጤቶችና ቀጣይ ስራዎች ላይ ትኩረት ያደረገ አውደ ጥናት በመካሄድ ላይ ነው።
በአውደ ጥናቱ ላይ የግብርና ሚኒስትር ዶክተር ግርማ አመንቴ፣ የጤና ሚኒስትር ደኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ ፣ የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ሽፈራው ተክለማሪያም ጨምሮ የልማት አጋሮች በመሳተፍ ላይ ናቸው።