በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቀጣይ 90 ቀናት የንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተከናወነ - ኢዜአ አማርኛ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቀጣይ 90 ቀናት የንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተከናወነ

አዲስ አበባ ፤ ጥር 21/2016 (ኢዜአ)፦ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከማዕከል እስከ ወረዳ ካሉት አመራሮች ጋር እስካሁን ያለዉን የስራ አፈፃፀም በመገምገም የቀጣይ 90 ቀናት የንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር መከናወኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት በህዝብ ተሳትፎ ከምንሰራቸዉ ስራዎች መካከል የስራ እድል ፈጠራ ፣የኑሮ ውድነትንና ገበያን ማረጋጋትን ፣የከተማ ግብርናን እና የሌማት ትሩፋት ቅድሚያ ሰጥተናቸዋል ሲሉ ገልጸዋል።
ከንቲባ አዳነች አክለውም ጥንካሬዎችን በማላቅ፣ ክፍተቶችን በመሙላት ቃላችንን ጠብቀን በትጋት ማገልገላችንን እንቀጥላለን ብለዋል።