የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትን የ 82 ዓመት ጉዞ የሚዳስስ አውደ ርእይ ተከፈተ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትን የ 82 ዓመት ጉዞ የሚዳስስ አውደ ርእይ ተከፈተ
አዲስ አበባ፣ ጥር 21/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ያስመረቀውን አዲስ የሚዲያ ኮምፕሌክስ መነሻ በማድረግ የ 82 አመት ጉዞውን የሚዳስስ አውደ ርእይ ተከፍቷል።
አንጋፋው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት(ኢዜአ) ያስገነባውን ዘመናዊ የሚዲያ ኮምፕሌክስ በዛሬው እለት አስመርቋል።
በምርቃት ሥነ-ስርዓቱ ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉን ጨምሮ ሌሎችም ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የሚዲያ አመራሮችና ሌሎችም እንግዶች ተገኝተዋል።
በአውደ ርዕዩ ኢዜአ ከሞርስ ኮድ ጀምሮ ዘመኑ የደረሰበትና ተቋሙ በአሁኑ ወቅት የሚጠቀምባቸው የድሮን ቴክኖሎጂና ሌሎች የቴክኖሎጂ ውጤቶች ለእይታ ቀርበዋል።
የሚዲያ ኮምፕሌክሱ ዘመኑ የደረሰበትን የሚዲያ ቴክኖሎጂ ያሟላ ሲሆን ሦስት የቴሌቪዥንና አራት የሬዲዮ ዘመናዊ ስቱዲዮዎችን አካቷል።
ከተመሠረተ 82 ዓመታት የሆነው አንጋፋው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) ብሔራዊ መግባባት የመፍጠርና የሀገር ገፅታ ግንባታ ተልዕኮውን ለማሳካት ዜና እና ዜና ነክ መረጃዎችን ተደራሽ በማድረግ ላይ ይገኛል።