ዘመኑ የደረሰበትን የሚዲያ ቴክኖሎጂ ያሟሉት የኢዜአ ዘመናዊ ስቱዲዮዎች ተጎበኙ - ኢዜአ አማርኛ
ዘመኑ የደረሰበትን የሚዲያ ቴክኖሎጂ ያሟሉት የኢዜአ ዘመናዊ ስቱዲዮዎች ተጎበኙ
አዲስ አበባ፤ ጥር 21/2016(ኢዜአ)፦ ዘመኑ የደረሰበትን የሚዲያ ቴክኖሎጂ ያሟሉት የኢዜአ ዘመናዊ ስቱዲዮዎች ተጎበኙ።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ያስገነባው ዘመናዊ የሚዲያ ኮምፕሌክስ በዛሬው ዕለት ተመርቋል።
ከምርቃቱ ጎን ለጎን የኢዜአ የሚዲያ ኮምፕሌክስ በእንግዶች ተጎብኝቷል።
በጉብኝቱ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፣ የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የኮሙኒኬሽን ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ፣ ሚኒስቴሮች፣ የሚዲያ አመራሮችን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
የኢዜአ የሚዲያ ኮምፕሌክስ ዘመኑ የደረሰበትን የሚዲያ ቴክኖሎጂ ያሟላ ስለመሆኑም ተገልጿል።
በዚህም እንግዶቹ የቴሌቪዥንና የሬዲዮ ዘመናዊ ስቱዲዮዎችን፣ ዘመናዊ ጅምናዚየምን ጨምሮ ሌሎች ግንባታዎችን ጎብኝተዋል።
የኢዜአ የሚዲያ ኮምፕሌክስ ሶስት የቴሌቪዥን እና አራት የሬዲዮ ስቱዲዮዎችን አካቷል።
በተጨማሪም ለቢሮ አገልግሎት የሚሆኑ በርካታ ክፍሎች፣ የመሰብሰቢያ አዳራሾች ቤተ-መጽሀፍት፣ የመዝናኛ ማዕከልና ዘመናዊ ጂምናዝየምም አሉት።