ቅዱስ ጊዮርጊስ በድሬዳዋ ከተማ ተሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
ቅዱስ ጊዮርጊስ በድሬዳዋ ከተማ ተሸነፈ
አዲስ አበባ፤ ጥር 18/2016(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ 12ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ በድሬዳዋ ከተማ 3 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት ተሸነፈ።
የድሬዳዋ ከተማን የማሸነፊያ ግቦች ኤፍሬም አሻሞ ፣ ሱራፌል ጌታቸው እና ቻርልስ ሙሴጌ አስቆጥረዋል ፡፡
ቅዱስ ጊዮርጊስ የዛሬውን ጨምሮ በውድድር አመቱ ሶስተኛውን ሽንፈት አስተናግዷል።
ውጤቱን ተከትሎ ድሬዳዋ ከተማ በ14 ነጥብ በሊጉ 10ኛ ደረጃን ሲይዝ ቅዱስ ጊዮርጊስ ደግሞ በ21 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣል።
ሊጉን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ29 ነጥብ ሲመራው መቻል በ27 ነጥብ ይከተላል፡፡