ቀጥታ፡

ኢምባሲዎች አድማሱና አውዱ የሰፋ የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል - አቶ ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ ፤ ጥር 18/2016(ኢዜአ)፦ኢምባሲዎች አድማሱና አውዱ የሰፋ የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን አሳሰቡ።

አቶ ደመቀ ዛሬ በተጠናቀቀው ዓመታዊ የአምባሳደሮች ጉባኤ ላይ የስራ መመሪያ በሰጡበት ወቅት የሚሲዮኖችን አድማስ ከፍ በማድረግ የኢትዮጵያ ተፈላጊነት ተደራሽነትና ተደማጭነት እንዲጨምር ለማድረግ መስራት እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።


 

ከአገሮች ጋር ያለን የሁለትዮሽ ግንኘነት እንዲጠናከር እና የባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲያችን እንዲሰፋ በማድረግ የአገራችንን ብሄራዊ ጥቅም ማረጋገጥ ይገባል ማለታቸውንም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም