ሕንድና ፈረንሳይ የጦር መሳሪያዎችን በጋራ ለማምረት ተስማሙ

1659

አዲስ አበባ ፤ጥር 18/2016(ኢዜአ)፡- ሕንድ እና ፈረንሳይ የጦር መሳሪያዎችን በጋራ ለማምረት መስማማታቸው ተገለጸ።

ስምምነቱ የተደረሰው የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በህንድ የአንድ ቀን የስራ ጉብኝት ማካሄዳቸውን ተከትሎ ነው።

በቆይታቸውም ከጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ እንዲሁም ከፕሬዚዳንት ድራኡፓዲ ሙርሙ ጋር የሁለትዮሽ ምክክር ያካሄዱ ሲሆን ሕንድ እና ፈረንሳይ የጦር መሳሪያዎችን በጋራ ለማምረት የሚያስችላቸውን ስምምነት መፈጸማቸው ተገልጿል።

ሀገራቱ የተስማሙት ለህንድ ብሎም ለተለያዩ ሀገራት የሚውሉ ሄሊኮፕተሮችን፣ ሰርጓጅ መርከቦችን እና ሌሎች የጦር መሳሪያዎችን በጋራ ለማምረት ነው።

በተጨማሪም በኒኩሌር ሃይል፣ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ምርምር ፣ በአየር ንበረት ለውጥ፣ በጤናና ግብርና ዘርፎች በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት እንደፈጸሙ ሮይተርስ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም