የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና አተገባበርን የሚዳስስ ምክክር መካሄድ ጀመረ

1177

 

አዲስ አበባ፤ ጥር 17/2016(ኢዜአ) ፦ “የአፍሪካ ብልጽግና ምክክር” በሚል መሪ ሀሳብ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና የአተገባበር ሁኔታን የሚዳስስ የመሪዎችና ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የምክክር መድረክ በጋና እየተካሄደ ነው።

ከዛሬ ጀምሮ ለሶሰት ቀናት የሚቆየው የምክክር መድረኩ የነጻ ንግድ ቀጣናው ወቅታዊ ሁኔታና የፕሮቶኮል አተገባበርን እንደሚገመግም ተመልክቷል።

የጋና መንግስትና አህጉራዊ ተቋማት በጋራ ባሰናዱት የምክክር መድረክ የሀገራት መሪዎችን ጨምሮ፣ የአህጉራዊና አለማቀፋዊ ተቋማት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት እንደሚሳተፉ የጋናው ግራፊክ ኦንላየን ዘግቧል።

በመድረኩ በነጻ ንግድ ቀጣናው ወቅታዊ አተገባበር የታዩ ክፍተቶችና መፍትሔያቸው እንደሚዳሰስም በመረጃው ተጠቁሟል።

ጎን ለጎንም አፍሪካዊ ምርቶች ለተሳታፊዎች ቀርበው አህጉራዊ የቢዝነስ ትስስር ለመፍጠር እንደታቀደም ነው በዘገባው የተመለከተው።


 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም