ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የኢትዮ ቻይና የኢንቨስትመንት ሴሚናርን አካሄደ

አዲስ አበባ፤ ጥር 16/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የኢትዮ ቻይና የኢንቨስትመንት ሴሚናርን አካሂዷል።

ሴሚናሩ በካውንስሉ ምክትል ሊቀ-መንበር ዛንግ ሻኦጋንግ ለተመራው ለቻይና የአለም አቀፍ የንግድ ፕሮሞሽን ካውንስል ልዑክ የተዘጋጀ መሆኑም ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ወይዘሮ ሀና አርአያስላሴ ቡድኑን ተቀብለው በኢትዮጵያ ባሉ ዘርፈ ብዙ የኢንቨስትመንት ዕድል እና አማራጮች ላይ ገለፃ አድርገዋል፡፡


 

የካውንስሉ ምክትል ሊቀ-መንበር ዛንግ ሻኦጋንግ የቻይና የአለም አቀፍ የንግድ ፕሮሞሽን ካውንስል ከኮሚሽኑ ጋር የጋራ የንግድ እና የኢንቨስትመንት ዘርፉን የማስተዋወቅ ስራ ለመስራት ያለውን ፍላጎትም ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ ሚኒስትር ኮንሶላር ያንግ ዪ ሃንግም ኤምባሲው ለጋራ ስራው ሙሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ ማረጋገጣቸውን ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡


 

ከኮሚሽኑ እና ከንግድ ምክር ቤት እንዲሁም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተውጣጡ ባለሙያዎች የኢንቨስትመንት ዘርፍን በተመለከተ ገላፃ አድርገዋል።

ከቡድኑ ለተነሱ ጥያቄዎችም በሃላፊዎች ምላሽ ተሰጥቷል፡፡

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን፣ የቻይና የአለም አቀፍ የንግድ ፕሮሞሽን ካውንስል እንዲሁም በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ የሁለቱን ሀገራት የንግድ እና የኢንቨስትመንት ግንኙነት ለማጠናከር በጋራ እንደሚሰሩም ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም