አቡነ ሉቃስ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 247 እና 251 ድንጋጌ ተላልፈዋል በሚል ክስ ተመሰረተባቸው - ኢዜአ አማርኛ
አቡነ ሉቃስ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 247 እና 251 ድንጋጌ ተላልፈዋል በሚል ክስ ተመሰረተባቸው

አዲስ አበባ፤ ጥር 16/2016(ኢዜአ)፦ አቡነ ሉቃስ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 247 እና 251 ድንጋጌ ተላልፈዋል በሚል ክስ ተመሰረተባቸው፡፡
ክሱ የቀረበባቸው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ ሕገ መንግስታዊና በሕገ መንግስት ሥርዓት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀል ጉዳዮች ችሎት ነው።
በአቡነ ሉቃስ ላይ ሁለት ክሶችን ያቀረበው የፍትሕ ሚኒስቴር የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጀነራል ዐቃቤ ሕግ ነው፡፡
ይህም ተከሳሽ አቡነ ሉቃስ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 247 (ሐ) እና አንቀጽ 258(ሀ) ስር የተደነገገውን ድንጋጌ እንዲሁም የወንጀል ህግ አንቀጽ 251 (ሐ) እና አንቀጽ 258 ስር የተመላከተውን ድንጋጌ ተላልፈዋል የሚሉ ሁለት ክሶች ናቸው የተመሰረቱባቸው።
በተጨማሪም ተከሳሹ በፀረ ሰላም ሃይሎች የሚፈፀሙ የወንጀል ተግባሮችን ተከትሎ መንግስት ፈፃሚዎችን ለሕግ ለማቅረብ እና ሕግ ለማስከበር የሚያደርጋቸውን ጥረቶች ለማደናቀፍ እና ሕዝብ መንግስት ላይ እምነት እንዲያጣ ማነሳሳታቸው በክሱ ተመላክቷል።
የክስ ዝርዝሩ የደረሰው ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ በጥር 27 ቀን 2016 ዓ.ም እንዲቀርቡ ትዕዛዝ በመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን ኤፍቢሲ ዘግቧል።