የኢትዮጵያ አየር መንገድ የብሪክስ አባል ሀገራት የንግድና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት የ2024 ሽልማትን አሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የብሪክስ አባል ሀገራት የንግድና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት የ2024 ሽልማትን አሸነፈ
አዲሰ አበባ፤ ጥር 14/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በየዓመቱ በሚከናወነው የብሪክስ አባል ሀገራት የንግድ እና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት የ2024 ሽልማት ላይ “Corporate Sustainability Achievement Award” አሸናፊ ሆኗል።
ሽልማቱ በብሪክስ አባል ሀገራት መካከል ለሚኖረው የንግድ ትስስር፣ የአፈፃፀም ልህቀት እና ፈጠራ ዕውቅና የሚሰጥ እንደሆነም ተገልጿል።
የብሪክስ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት በአባል ሀገራት ውስጥ የሚገኙ የንግድና የኢንዱስትሪ እንቅስቃሴዎችን ለማበረታታት በፈረንጆቹ 2012 የተቋቋመ ምክር ቤት መሆኑን ከአየር መንገዱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡