ቀጥታ፡

አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር  ማይክ ሀመር ጋር ተወያዩ

 

አዲስ አበባ፤ ጥር 14/2016(ኢዜአ)፡- የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሀመርን  በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

አምባሳደር ምስጋኑ በዚህ ወቅት እንዳሉት ኢትዮጵያና አሜሪካ ዘመናትን ያስቆጠረ ጠንካራ እና ቁልፍ ግንኙነት ያላቸው አጋር ሀገራት ናቸው።

አምባሳደሩ አክለውም የኢትዮጵያ መንግሥት ዘላቂ ሰላምን በመገንባት ረገድ እያከናወነ ያለውን ዘርፈ ብዙ ተግባራት በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል።

በተጨማሪም ሁለቱ ወገኖች በአህጉራዊና አለማቀፋዊ የጋራ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም