ቀጥታ፡

የብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚዬምን ጎበኙ

አዲስ አበባ ጥር 14/ 2016(ኢዜአ)፦ የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚዬምን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡


 

የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ በትናንትናው ዕለት መካሄድ መጀመሩ ይታወሳል፡፡

በ3 ነጥብ 3 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው እና ባለ አምስት ወለሉ ፕሮጀክት የአድዋን ድል፣ የኢትዮጵያውያንን ጀግኖች፣ የአድዋን መልክዓምድር በሚወክል መልኩ እየተገነባ ይገኛል።

የአድዋ ጦርነት እና የድል ክፍለ ታሪክን ከቦታ ጋር አዛምዶ መያዙም እና የአድዋን ሰንሰለታማ ተራሮች፣ የፈረሰኞች ፣ ለሴት ጀግኖች ክብር የተሰየመ ማስታወሻ፣ የአንድነት ማዕከል፣ የአፍሪካ ነፃነት ማስታወሻ እንዲሁም የኢትዮጵያ ጀግኖች ጉዞና 5 የመግቢያ በሮች እንዳሉት ተመላክቷል።

በውስጡም የከተማ አስተዳደሩ ምክርቤት አዳራሽን ጭምሮ ከ2 ሺህ በላይ ሰዎችን የሚያስተናግድ አዳራሽ1 ሺህ መኪኖችን የሚያስተናግድ ፓርኪንግ፣ የመዝናኛ ሥፍራዎች የስፖርት ማዘውተሪያዎች ሲኒማ እና የኤግዚቢሽን አገልግሎትን ያካተተ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም