ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ዲፕሎማሲ አማካሪ ፎረም ተቋቋመ - ኢዜአ አማርኛ
ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ዲፕሎማሲ አማካሪ ፎረም ተቋቋመ
አዲስ አበባ ፤ ጥር 13/2016 (ኢዜአ)፡- ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ዲፕሎማሲ አማካሪ ፎረም በዛሬው እለት ተቋቁሟል ፡፡
ኢትዮጵያ ዳያስፖራውን በማሳተፍ ሂደት የገጠሟት ፈተናዎች፣ የተገኙ ውጤቶችና ቀጣይ ስራዎች ላይ ትኩረት ያደረገ የፓናል ውይይት በሳይንስ ሙዚየም ተካሂዷል፡፡
በዚሁ ጊዜም ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ዲፕሎማሲ አማካሪ ፎረም የተቋቋመው ሲሆን ፎረሙ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በአገር ልማት ላይ የበለጠ እንዲሳተፉ ለማድረግ ያለመ ነው፡፡
ፎረሙ ዳያስፖራው ምን ይፈልጋል፤ የዳያስፖራን ጥቅም ከማስከበር አኳያ ምን አይነት ስራዎች ሊከናወኑ ይገባል የሚለውን ከመንግሥት ጋር በመነጋር የሚሰራ ይሆናል ተብሏል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በተለያዩ የልማት መስኮች አበረታች ተሳትፎ እያደረጉ ነው፡፡
ይሄን ተሳትፎ ከፍ ወዳለ ደረጃ ማሸጋገር እንደሚገባ ጠቁመው መንግሥት ዳያስፖራ አባላት ተሳትፎ ማሳደግ ላይ ትኩረት ማድረጉን ገልጸዋል፡፡
በኢትዮጵያ ያሉ ችግሮች የሚፈቱት በጋራ ትብብር መሆኑን ጠቅሰው፤ አገር ግንባታ ላይ ምሁራን፣ በውጭ የሚኖሩ ዳያስፖራ አባላት ከመንግሥት ጋር የበለጠ በመቀራረብ ሚናቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል