የናይጄሪያዋ ሌጎስ ከተማ ለአንድ ግዜ አገልግሎት ብቻ የሚውሉ ፕላስቲኮችን አገደች   

1038


አዲስ አበባ ፤ጥር 13/2016(ኢዜአ)፦ የናይጄሪያዋ ሌጎስ ከተማ ለአንድ ግዜ አገልግሎት የሚውሉ ፕላስቲኮችንና ማሸጊያዎች ጥቅም ላይ እንዳይውሉ አገደች፡፡

የሌጎስ የአካባቢ ኮሚሽነር ቶክንቦ ዋሃብ እንዳሉት በግዜ ሂደት የማይበሰብሱ የፕላስቲክ ውጤቶች ዋነኛ የአካበቢ ብክለት መንስኤዎች ናቸው፡፡

በተጨማሪም የማይበሰብሱ የፕላስቲክ ውጤቶች ውሃ ማፋሰሻዎችንም በመዝጋት ለችግር ያጋልጣሉ ብለዋል፡፡

የሃገሪቱ ባላስልጣናት እንዳሉት በ2009 በካይ ፕላስቲክን በተመለከተ ወጥቶ ሳይፈፀም የቆየው  ህግ ተፈፃሚ እንዲሆንና በማይተገብሩት ላይ ቅጣት እንዲወሰንም አሳስበዋል፡፡ 

ሌጎስ በአፍሪካ በብክለት ደረጃ ከፍተኛ ከሚባሉት ከተሞች ውስጥ ትጠቀሳለች፡፡

በአለም አቀፍ ደረጃ ያሉ ባለሙያዎች ናይጄሪያ በአመት 2.5 ሚሊየን ቶን የሚገመት የፕላስቲክ ቆሻሻ እንደምታመነጭ መናገራቸውን  የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም