ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከኮሎምቢያ የዓለም ዋንጫ ውጭ ሆነ

አዲስ አበባ፤ ጥር 12/2016 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የመጨረሻ ዙር ጨዋታውን ዛሬ ከሞሮኮ አቻው ጋር በአዲስ አበባ አድርጓል፡፡

በአበበ ቢቂላ ስታዲየም የተደረገውን የመልስ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የሞሮኮ አቻውን 1 ለ 0 ቢያሸንፍም በድምር ውጤት 2 ለ 1 ተሸንፎ ከኮሎምቢያው የዓለም ዋንጫ ውጭ ሆኗል፡፡

ቡድኑ ባሳለፍነው ጥር 3 ቀን 2016 ዓ.ም ከሞሮኮ አቻው ጋር በአልጀዲዳ ከተማ ኤላብዲ ስታዲየም ያደረገውን የመጀመሪያ የደርሶ መልስ ጨዋታ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት መሸነፉ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የዛሬውን ጨዋታ በድምር ውጤት ቢያሸንፍ በቀጥታ ኮሎምቢያ ለምታዘጋጀው የ2024 ዓለም ዋንጫ ውድድር ማለፍ ይችል ነበር፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም