ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ለበዓለ ጥምቀቱ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ - ኢዜአ አማርኛ
ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ለበዓለ ጥምቀቱ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፤ ጥር 11/2016 (ኢዜአ)፦ የኢፌዴሪ ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለበዓለ ጥምቀቱ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።
በመልዕክታቸውም “ውድ የክርስትና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን እንኳን ለጥምቀት በዓል በደህና አደረሳችሁ “ ብለዋል።
በሃገራችን በአደባባይ ከሚከበሩት በዓላት አንዱ የሆነው ጥምቀት በድምቀትና በጽኑ መንፈሳዊ ስሜት የሚከበር ነው ያሉት ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ በዩኒስኮ የተመዘገበና ልንንከባከበው የሚገባ የዓለም ቅርስም ነው ሲሉም አክለዋል።
ኢትዮጵያውያን የጋራ ዓላማን ካወቁ፣ ካመኑ ከሚከፋፍላቸው በላይ የሚያስተሳሥራቸው እንደሚበልጥ በተደጋጋሚ አሳይተዋል፣ እያሳዩም ነው ሲሉም ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ገልጸዋል።
ጥምቀትን ኢትዮጵያውያንና ከዓለም ዙርያ ከሚመጡ በርካታ ቱሪስቶች ጋር እንደተለመደው እናክብረው በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል።
ቅርስነቱን የሚያቆየው በዓሉ በአግባቡ ሲከበር መሆኑን አንስተዋል።
ፈጣሪ ከሁላችን በላይ የሆነችውን ሃገራችንን አብዝቶ ይባርክልን፤ ሠላምን ያስፍንልን ብለዋል በመዕልክታቸው።