በተለያዩ ከተሞች ታቦታት ወደ ማደሪያ ስፍራቸው ደርሰዋል - ኢዜአ አማርኛ
በተለያዩ ከተሞች ታቦታት ወደ ማደሪያ ስፍራቸው ደርሰዋል
ዲላ/ሶዶ/አርባ ምንጭ/ጂንካ/ቦንጋ/ሚዛን አማን፣ አክሱም፣ ጥር 10/2016 (ኢዜአ)፦በአራት ክልሎች በሚገኙ ስምንት ከተሞች ታቦታት ወደ ማደሪያ ስፍራቸው ደርሰዋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በዲላ፣ በወላይታ ሶዶ፣ በአርባ ምንጭና ጂንካ፣በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በቦንጋና በሚዛን አማን፣ በኦሮሚያ ክልል በባሌ ሮቤና በትግራይ ክልል በአክሱም ከተሞች የከተራ በዓል ተከብሯል።
በከተሞቹ በዓሉ የተከበረው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች በታደሙበት በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች ነው።
በከተሞቹ የእምነቱ ተከታዮች በተለያዩ ባህላዊ አልባሳት ደምቀውና ተውበው እንዲሁም በተለያዩ ዝማሬዎች ከተለያዩ አድባራት የተወጣጡ ታቦታትን አጅበው ወደ ማደሪያ ስፍራቸው ሸኝተዋል።
ምዕመናን፣ ሰንበት ተማሪዎችና ካህናት በመንፈሳዊ ዝማሬዎች ታቦታቱን አጅበው ወደ ጥምቀተ ባህር ወርደዋል።
በአሁን ሰአት በሁሉም ከተሞች ታቦታት ወደ ማደሪያ ስፍራቸው ደርሰዋል።