የጥምቀት በዓል የሰላም ተምሳሌት ነው- የዋግ ኽምራ ሀገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ

ሰቆጣ፤ ጥር 10/2016 (ኢዜአ)፦ የጥምቀት በዓል የነፃነትና የሰላም ተምሳሌት መሆኑን የዋግ ኽምራ ሀገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ ሊቀ ህሩያን ሃይሌ አለሙ ገለጹ።

በሰቆጣ ከተማ የጥምቀት ከተራ በዓል የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ አቡነ በርናባስና ሌሎችም በርካታ የእምነቱ ተከታዮች በተገኙበት በደማቅ ሥነ-ሥርዓት ተከብሯል።

የዋግ ኽምራ ሀገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ ሊቀ ህሩያን ሃይሌ አለሙ ምእመኑ ሃይማኖታዊ ህብረ ዝማሬን በበገና፣ በፅናፅል፣ በከበሮ ታጅቦ በደመቀ መልኩ ታቦታቱን ወደ ማደሪያ ቦታቸው መድረሳቸውን ተናግረዋል።

የጥምቀት በዓል የነፃነትና የሰላም ተምሳሌት መሆኑን ገልጸው፤ ምእመኑ ሃይማኖታዊ ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ በዓሉን ማክበሩን አስረድተዋል።

ከበዓሉ ተሳታፊዎች መካከል ወጣት መኳንት ካሳ በሰጠው አስተያየት የከተራ በዓል በድምቀት ተከብሮ ማለፉ እንዳስደሰተው ገልጿል።

የጥምቀት በዓልም ሃይማኖታዊ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ ነገ በድምቀት ለማክበር መዘጋጀቱም ተናግሯል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም