ቀጥታ፡

"ያልተቋረጠው የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ታሪካዊ፣ ጂኦፖለቲካዊና ከባቢያዊ አተያይ" በሚል ርዕስ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ውይይት እየተካሄደ ነው

ሶዶ፤ ጥር 10/2016 (ኢዜአ)፦በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ "ያልተቋረጠው የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ታሪካዊ፣ ጂኦፖለቲካዊና ከባቢያዊ አተያይ" በሚል ርዕስ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው። 

የውይይት መድረኩ ዋና ትኩረቱን ያደረገው በኢትዮጵያና ቀይ ባህር ታሪካዊ ክንዋኔዎች እንዲሁም የባህር በር ጥያቄው ሞራላዊና ህጋዊ ጉዳዮችን በተመለከተ መሆኑም ተጠቁሟል። 

ለአንድ ቀን በተዘጋጀው መድረክም በተለያዩ ምሁራን ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

በመድረኩም የዩኒቨርሲቲው አመራሮችና ምሁራን፣ የወላይታ ዞንና ወረዳ አመራሮች እንዲሁም የሀይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ታድመዋል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም