ቀጥታ፡

አምባሳደሮች በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ድርድር እና በዓባይ ወንዝ አጠቃቀም ላይ ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ ጥር 9/2016 (ኢዜአ) በተለያዩ ሀገራት የኢትዮጵያ አምባሳደሮች በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ድርድር እና በዓባይ ወንዝ አጠቃቀም ላይ ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ የኢትዮጵያ ታላቁ ሕዳሴ ግድብ ዋና ተደራዳሪ አምባሳደር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ  እና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዓለም አቀፍ ህግ ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ረታ አለሙ በኢትዮጵያ፣ ግብፅ እና ሱዳን መካከል የተካሄደውን ተከታታይ የሦስትዮሽ ድርድር አስመልክተው ማብራሪያ ሰጥተዋል።


 

አምባሳደሮቹ ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ውሃ ፍትሃዊ እና ምክንያታዊ የሆነ አጠቃቀም መርሕ ላይ ያላትን እምነት እና በመሠረታዊ መርሆዎች መግለጫ ላይ የተመለከቱትን መብቶች እና ግዴታዎች አስረድተዋል።

ኢትዮጵያ የሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ጥቅም ለማስከበር ያላትን ጽኑ አቋም መግለጻቸውንም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም