ለ18ኛው የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል መሳካት አስተዋፅኦ ላደረጉ አካላት የእውቅና መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
ለ18ኛው የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል መሳካት አስተዋፅኦ ላደረጉ አካላት የእውቅና መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፤ ጥር 9/2016 (ኢዜአ)፦በሶማሌ ክልል ጀግጅጋ ለተከበረው 18ኛው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል መሳካት አስተዋፅኦ ላደረጉ አካላት የእውቅና መስጠት መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።
በመርሐ ግብሩ ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፣ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሁመድ፣ የፌደራልና የክልል የስራ ኃላፊዎች፣ የመገናኛ ብዙኃን አመራሮች ተገኝተዋል።
አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ በዓሉ ህዝቦችን የበለጠ ከማቀራረብ እና ህብረ ብሔራዊ አንድነትን በማጠናከር ረገድ ትልቅ ሚና ተጫውቷል ነው ያሉት።
ለበዓሉ በስኬት መካሄድ የሶማሌ ክልል አመራር፣ የፌደራልና የክልል ጸጥታ መዋቅር እንዲሁም መገናኛ ብዙሃን የላቀ ሚና በማበርከታቸው ምስጋና አቅርበዋል።
በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው የእውቅና አሰጣጥ መርሐ ግብር ላይ 18ኛው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረቦች በዓል አከባበር አጠቃላይ ገጽታና የተገኙ ውጤቶች ለተሳታፊዎች ቀርበዋል።