በአዲስ አበባ በሚቀጥሉት ስድስት ወራት 10 ተንቀሳቃሽ የአየር ብክለት መከታተያ ጣቢያዎች ይተከላሉ - ኢዜአ አማርኛ
በአዲስ አበባ በሚቀጥሉት ስድስት ወራት 10 ተንቀሳቃሽ የአየር ብክለት መከታተያ ጣቢያዎች ይተከላሉ
አዲስ አበባ፤ ጥር 9/2016 (ኢዜአ)፦በአዲስ አበባ በሚቀጥሉት ስድስት ወራት 10 ተንቀሳቃሽ የአየር ብክለት መከታተያ ጣቢያዎች እንደሚተከሉ የኢትዮጵያ ሚትዎሮሎጂ ኢኒስቲትዩት ገለጸ።
የአየር ትንበያን መረጃ ትክክለኛነትና ወቅታዊነትን የሚያሳድጉ ቴክኖሎጂዎችን ማስፋፋት ላይ ትኩረት ማድረጉንም ኢኒስቲትዩቱ አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ሚትዎሮሎጂ ኢኒስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክንፈ ኃይለማርያም ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ ኢኒስቲትዩቱ መረጃ የመሰብሰብና የመተንተን አቅሙን ለማሳደግ የሚያግዙ ቴክኖሎጂዎች ላይ ትኩረት አድርጓል።
ኢኒስቲትዩቱ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችን ጨምሮ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ፕሮጀክቶችን ቀርጾ ወደ ስራ ገብቷል፡፡
በዚህም የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያዎችን ደረጃ በማሻሻል፣ ቁጥራቸውን በማሳደግና ውጤታማነታቸውን ከፍ በማድረግ በኩል ተጨባጭ እንቅስቃሴዎች እያካሄደ መሆኑን ተናግረዋል።
ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ እንዳሉት፤ ከፊንላንድ መንግሥት በተገኘ ብድርና እርዳታ ሦስት ተጨማሪ የአየር ሁኔታ መከታተያ ራዳር እና አራት የመብረቅ መከታተያ ጣቢያዎችን ወደ ሥራ ለማስገባት እንቅቃሴዎች ተጀምረዋል።
በተለይም በሚቀጥሉት ስድስት ወራት በአዲስ አበባ አስር የአየር ብክለት መከታተያ ጣቢያዎች እንደሚተከሉ ጠቅሰዋል፡፡
እንደ ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ገለጻ ተጨማሪ ሦስት የአየር ሁኔታ መከታተያ ራዳር ሥራ ላይ ለማዋል እንቅስቃሴ የተጀመረ ሲሆን ከሦስቱ ውስጥ አንዱ በአማራ ክልል እነዋሪ ላይ ሙሉ በሙሉ የተከላው ሥራው መጠናቀቁን ገልጸዋል።
የአየር ሁኔታ መከታተያ ራዳሮቹ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን የሚጠቀሙ በመሆኑ ጎርፍንና በረዶን ለመከታተል ፣ የዝናብና የደመና መረጃዎችን ለማግኘት ይረዳሉ ብለዋል፡፡
እንዲሁም ደመና የማበለጸግ ቴክኖሎጂን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል መረጃ ለመሰብሰብ ትልቅ ሚና ያላቸው መሆኑን አብራርተዋል።
ኢኒስቲትዩቱ ባከናወነው የስቴሽን ማስተር ፕላን ጥናት መሰረት 2 ሺህ 800 የመሬት ላይና ፣8 የከፍታ አየር ጣቢያዎች ፣12 የአየር ብክለት መከታተያ ራዳር እንደሚያስፈልግ መለየቱን አስረድተዋል።
የሰው አልባ ጣቢያዎችን ቁጥር ከፍ ለማድረግ በተሰራው ሥራ ቁጥራቸውን 280 ማድረስ መቻሉን ጠቁመው በሚቀጥሉት አስር ዓመታት በሰው የሚሰሩ ጣቢያዎችን ሙሉ በሙሉ ወደ በሰው አልባ ጣቢያዎች ለመተካት ግብ ተይዟል ብለዋል።
ለአብነትም ኢኒስቲትዩቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ መረጃ የሚለዋወጥባቸው 17 ሳይኖፕቲክ ጣቢያዎች ያሉት ቢሆንም ጣቢያዎቹ ሙሉ በሙሉ በሰው የሚሰሩ ናቸው ሲሉም አክለዋል።
የአየር ትንበያን መረጃ ትክክለኛነትና ወቅታዊነትን የሚያሳድጉ ቴክኖሎጂዎችን ማስፋፋት ላይ ትኩረት ማድረጉንም ኢኒስቲትዩቱ አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ሚትዎሮሎጂ ኢኒስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክንፈ ኃይለማርያም ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ ኢኒስቲትዩቱ መረጃ የመሰብሰብና የመተንተን አቅሙን ለማሳደግ የሚያግዙ ቴክኖሎጂዎች ላይ ትኩረት አድርጓል።
ኢኒስቲትዩቱ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችን ጨምሮ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ፕሮጀክቶችን ቀርጾ ወደ ስራ ገብቷል፡፡
በዚህም የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያዎችን ደረጃ በማሻሻል፣ ቁጥራቸውን በማሳደግና ውጤታማነታቸውን ከፍ በማድረግ በኩል ተጨባጭ እንቅስቃሴዎች እያካሄደ መሆኑን ተናግረዋል።
ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ እንዳሉት፤ ከፊንላንድ መንግሥት በተገኘ ብድርና እርዳታ ሦስት ተጨማሪ የአየር ሁኔታ መከታተያ ራዳር እና አራት የመብረቅ መከታተያ ጣቢያዎችን ወደ ሥራ ለማስገባት እንቅቃሴዎች ተጀምረዋል።
በተለይም በሚቀጥሉት ስድስት ወራት በአዲስ አበባ አስር የአየር ብክለት መከታተያ ጣቢያዎች እንደሚተከሉ ጠቅሰዋል፡፡
እንደ ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ገለጻ ተጨማሪ ሦስት የአየር ሁኔታ መከታተያ ራዳር ሥራ ላይ ለማዋል እንቅስቃሴ የተጀመረ ሲሆን ከሦስቱ ውስጥ አንዱ በአማራ ክልል እነዋሪ ላይ ሙሉ በሙሉ የተከላው ሥራው መጠናቀቁን ገልጸዋል።
የአየር ሁኔታ መከታተያ ራዳሮቹ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን የሚጠቀሙ በመሆኑ ጎርፍንና በረዶን ለመከታተል ፣ የዝናብና የደመና መረጃዎችን ለማግኘት ይረዳሉ ብለዋል፡፡
እንዲሁም ደመና የማበለጸግ ቴክኖሎጂን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል መረጃ ለመሰብሰብ ትልቅ ሚና ያላቸው መሆኑን አብራርተዋል።
ኢኒስቲትዩቱ ባከናወነው የስቴሽን ማስተር ፕላን ጥናት መሰረት 2 ሺ 800 የመሬት ላይና ፣8 የከፍታ አየር ጣቢያዎች ፣12 የአየር ብክለት መከታተያ ራዳር እንደሚያስፈልግ መለየቱን አስረድተዋል።