አብዝቶ የአልኮል መጠጥ በወሰደ መንገደኛ ምክንያት ጉዞውን ያቋረጠው አውሮፕላን 

975

አዲስ አበባ፤ ጥር 9/2016(ኢዜአ)፦ አብዝቶ የአልኮል መጠጥ የወሰደ ጎልማሳ በፈጠረው ረብሻ ከጃፓን ወደ አሜሪካ ይጓዝ የነበረ አውሮፕላን በረራ መቋረጡ ተነገረ።

በአውሮፕላኑ ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ አልኮል ጠጥቶ የተገኘው የ55 አመት አሜሪካዊው ጎልማሳ መሆኑን የኤኤንኤ አየር መንገድ ቃል አቀባይ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ተናግረዋል።

ግለሰቡ  በአውሮፕላን ውስጥ በመረበሽና የበረራ አስተናጋጅን  ክርን በመንከሱ በረራው እንዲቋረጥ መገደዱን ገልጸዋል።

159 ተሳፋሪዎችን ይዞ ፓስፊክ ውቂያኖስ የደረሰው አውሮፕላን በረራውን አቋርጦ ወደ ቶክዮ ሃኔዳ አየር ማረፊያ መመለሱን ነው የገለጹት።
 
ይህ አይነቱ ክስተት በጃፓን እየተለመደ መምጣቱን ያነሳው ዘገባው ከጥቂት ሳምንታት በፊት በሀገር ውስጥ በረራ የኤኤንኤ ንብረት የሆነ አውሮፕላን መስኮት በመሰንጠቁ በረራ መቋረጡን አስታውሷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም