ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ የተፈራረሙት የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት የቀጣናውን ሁለንተናዊ እድገት የሚያፋጥን ነው-- የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት

አዲስ አበባ፤ ጥር 8/2016(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ የተፈራረሙት የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት የቀጣናውን ሁለንተናዊ እድገት የሚያፋጥን መሆኑን የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት አስታወቀ፡፡ 

ምክር ቤቱ ኢትዮጵያ እና ሱማሌላንድ የተፈራረሙት የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት በተመለከተ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥቷል።

የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ፉአድ ገና ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት ከሱማሌላንድ ጋር ያደረገችው የመግባቢያ ሰነድ የስምምነት ፊርማ ሰላማዊና ዲፕሎማሲያዊ  ሂደትን የተከተለ መሆኑን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ እና ሱማሌላንድ የተፈራረሙት የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት የጋራ ተጠቃሚነትን መሰረት ያደረገና የቀጣናውን ሁለንተናዊ እድገት የሚያፋጥን መሆኑንም ነው የተናገረው፡፡

በተጨማሪም የኢትዮጵያን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴ በማፋጠን ረገድ ጉልህ ሚና እንዳለው ተናግረዋል።

ምክር ቤቱ ዓላማ አድርጎ ከተመሰረተባቸው አንኳር አጀንዳዎች ውስጥ የኢትዮጵያን ጥቅም ለማጠበቅ በሚሰሩ ስራዎች ወጣቶች የነቃ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ማስቻል መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

በአጠቃላይ ምክር ቤቱ በኢትዮጵያ እና ሱማሌላንድ መካከል የተፈረመውን የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት እንደሚደግፍና ስምምነቱም የወጣቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ እንደሚረዳ አመልክተዋል።

ስምምነቱ ለኢትዮጵያ ከሚኖረው ፋይዳ አኳያ ለስኬታማነቱ ምክር ቤቱ  የበኩሉን ሚና እንደሚወጣም ገልጸዋል።

  

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም