ቀጥታ፡

አዲስ አበባን ሕጻናት በአካልና በአዕምሮ ተገንብተው የሚያድጉባት ምርጥ አፍሪካዊት መዲና ለማድረግ በትጋት መስራታችንን እንቀጥላለን - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፤ ጥር 7/2016(ኢዜአ)፦ አዲስ አበባን ሕጻናት ቦርቀው፣ በአካልና በአዕምሮ ተገንብተው የሚያድጉባት ምርጥ አፍሪካዊት መዲና ለማድረግ በትጋት መስራታችንን እንቀጥላለን ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።


 

የትውልድ ግንባታ ስራ የሆነውን “የቀዳማይ ልጅነት ልማት ፕሮግራም“ ለማገዝ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ከዩኒሴፍ ጋር መፈራረማቸውን ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል።

“ከዩኒሴፍ የኢትዮጵያ ተወካይ ዶክተር አቡበክር ካምፖ ጋር የተፈራረምነው የመግባቢያ ስምምነት ከገነባናቸው የሕጻናት መዋያ እንዲሁም የመጫወቻና መዝናኛ ማዕከላት በተጨማሪ የሕጻናት የጤና አገልግሎት ማሻሻያ ላይ እያደረግን ያለውን ስራ የሚያግዝ ይሆናል” ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም