ቀጥታ፡

የገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገር እና ገበታ ለትውልድ ሥራዎች የግሉ ዘርፍ በመዳረሻዎችና አገልግሎቶች ላይ በይበልጥ እንዲሰማራ መንገድ ለመክፈት ታልመው የተሰሩ ናቸው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ ጥር 7/2016(ኢዜአ)፦ የገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገር እና ገበታ ለትውልድ ሥራዎች የግሉ ዘርፍ መዳረሻዎችና አገልግሎቶች ላይ በይበልጥ እንዲሰማራ መንገድ ለመክፈት ታልመው የተሰሩ ናቸው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ቱሪዝም ከአምስቱ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ምሦሦዎች አንዱ እንደመሆኑ መጠን የግሉ ዘርፍ ወሳኝ ሚና እንዳለው እንገነዘባለን ብለዋል። 

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም በዘርፉ የሚደረጉ የገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገር እና ገበታ ለትውልድ ሥራዎች የግሉ ዘርፍ መዳረሻዎችንና አገልግሎቶችን በይበልጥ እንዲሰማራ መንገድ ለመክፈት ታልመው የተሰሩ ናቸው ሲሉም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም