የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጋር ምክክር አካሄደ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጋር ምክክር አካሄደ
አዲስ አበባ፤ ጥር 6/2016 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች ከኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ እና ከሌሎች የኮሚሽኑ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ምክክር አካሂደዋል።
ኮሚሽኑ ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ በተለያዩ ክልሎች ተንቀሳቅሰው የተሳካ ስራዎችን እንደሰሩ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አመራሮች ገልጸዋል።
በዚህም የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ተገቢውን ድጋፍ እንዳደረገላቸው አስታውሰው በቀጣይም የሚካሄዱ የምክክር መድረኮች በሰላም እንዲካሄዱ ትብብሩ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት መናገራቸውን ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል በበኩላቸው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የሚያካሂዳቸውን የምክክር መድረኮች ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲካሄዱ በትብብር ለመስራት በተደረገው ውይይት ላይ መስማማታቸውን ገልፀዋል።