ከ 100 በላይ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በቻይና መንግስት የተመቻቸ የስኮላርሽፕ እድል አገኙ

638

አዲስ አበባ ፤ ጥር 6/2016 (ኢዜአ)፡- 143 በተለያየ የትምህርት መስክ ላይ ያሉ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በቻይና መንግስት የተመቻቸ የስኮላርሽፕ እድል አገኙ፡፡ 

የቻይና ኢትዮጵያ የስኮላርሽፕ ወዳጅነት ማብሰሪያ ስነስርአት ላይ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሳሙኤል ክፍሌ(ዶ/ር) እንደተናገሩት የቻይና መንግስትና ዩኒቨርሲቲዎች ከአዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ ጋር ጠንካራ እና ትርጉም ያለው ትብብር አላቸው ፤ፋካልቲዎችንና ተማሪዎችንም እያሰለጠኑ ነው ብለዋል፡፡

በቻይና እና በኢትዮጵያ የትምህርት አካዳሚዎች መካከል ያለው ትብብር የቻይና ኢትዮጵያ ግንኙነትን የሚያጠናክር መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ 

በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣኦ ዢዩዋን በበኩላቸው የስኮላርሽፕ እድሉ ተጠቃሚ ኢትዮጵያውያን ለሃገራቸው  ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገት አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ያስችላቸዋል፡፡

የአዲስ አባባ የኒቨርሲቲና ምሩቃኑ በቻይና ኢትዮጵያ ግንኙነት በጎ አስተዋፅኦ አበርክተዋል ያሉ ሲሆን በቀጣይም እንዲጠናከር አዲስ አበባ የኒቨርስቲ እንደ ድልድይ ሆኖ እንዲሰራ ጠይቀዋል፡፡

ስኮላርሽፕ ካገኙት ኢትዮጵያውያን መካከል ሙሉጌታ አየለ በሰጠው አስተያየት እድሉን ያገኘን ኢትዮጵያውያን  ትምህርታችንን ለማሳደግና በሀገራችን ልማት ላይ ለመሳተፍ ያስችለናል ብሏል፡፡

የቻይና ኢትዮጵያ የስኮላርሽፕ ወዳጅነት ማብሰሪያ በተካሄደ ስነስርአት ላይ  በቻይንኛ  ቋንቋ ክህሎት የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ 22 ኢትዮጵያውያን መሸለማቸውንም ፒፕልስ ዴየሊ ኦንላየን ድረገፅ ዘግቧል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም