በ41ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል ሀገር አቋራጭ ውድድር በሴቶች ንግድ ባንክ በወንዶች ሸገር ከተማ አሸነፉ - ኢዜአ አማርኛ
በ41ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል ሀገር አቋራጭ ውድድር በሴቶች ንግድ ባንክ በወንዶች ሸገር ከተማ አሸነፉ
አዲስ አበባ፤ ጥር 5/2016 (ኢዜአ)፦ በ41ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል ሀገር አቋራጭ ውድድር በሴቶች ንግድ ባንክ በወንዶች ሸገር ከተማ አሸንፈዋል።
41ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል ሀገር አቋራጭ ውድድር መጠናቀቁን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡
በውድድሩ ላይ በተካሄደው የ6 ኪሎ ሜትር የወጣት ሴቶች ሩጫ አትሌት የኔዋ ንብረት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስታሸንፍ፤ አሳየች አድነው ከንግድ ባንክ 2ኛ እንዲሁም ሽቶ ጉሚ ከኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኢንጅነሪንግ 3ኛ ደረጃን ይዘው ውድድሩን አጠናቀዋል፡፡
እንዲሁም በ8ኪሎ ሜትር የወጣት ወንዶች ውድድር አትሌት አቤል በቀለ ከሸገር ከተማ ቀዳሚ በመሆን አሸንፏል፡፡
በዚሁ የውድድር መርሐ-ግብር የኢትዮ ኤሌክትሪኮቹ አትሌት ሳሙኤል ፍሬው 2ኛ ሲወጣ አትሌት ጀንበሩ ሲሳይ 3ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን ማጠናቀቃቸውን ፌዴሬሽኑ አስታውቋል፡፡