አንጋፋው ጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ - ኢዜአ አማርኛ
አንጋፋው ጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
አዲስ አበባ፤ ጥር 5/2016(ኢዜአ)፦አንጋፋው ጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።
ጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ ሕክምናውን በአሜሪካን ሀገር ሲከታተል የነበረ ሲሆን በዛሬው ዕለት ሕይወቱ አልፏል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ እና ለአድናቂዎቹ መፅናናትን ይመኛል።