የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ግብር በታማኝነት ለከፈሉ 562 ግብር ከፋዮች ዕውቅናና ሽልማት ሊሰጥ ነው

አዲስ አበባ ፤ ጥር 3/2016 (ኢዜአ)፦የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ለአራተኛ ጊዜ የሚጠበቅባቸውን ግብር በታማኝነት ለከፈሉ 562 ግብር ከፋዮች ዕውቅናና ሽልማትሊስጥ ነው፡፡  

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የሕግ ተገዥነት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ኮማንደር መሃመድ አህመድ በሰጡት መግለጫ፤ ከዚህ ቀደም ለሦስት ተከታታይ ጊዜ ለታማኝ ግብር ከፋዮች ዕውቅናና ሽልማት ተሰጥቷል ብለዋል።

አሁን ደግሞ ለአራተኛ ጊዜ የሚጠበቅባቸውን ግብር በታማኝነት ለከፈሉ 562 ግብር ከፋዮች ዕውቅናና ሽልማት ጥር 5/2016 ዓ.ም ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት መርኃ ግብር የሚሰጥ መሆኑ ገልጸዋል።
 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም