የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ/ኢዜማ/ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ አባላት የዓድዋ ድል ሙዚየምን ጎብኙ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ/ኢዜማ/ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ አባላት የዓድዋ ድል ሙዚየምን ጎብኙ
አዲስ አበባ፤ ጥር 2/2016(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ/ኢዜማ/ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ አባላት የዓድዋ ድል ሙዚየምን ጎብኝተዋል::
የዓድዋ ድል ሙዚየም የዓድዋን ታሪክ ቀጣዩ ትውልድ በበቂ ሁኔታ እንዲገነዘበው የሚያስችል መሆኑን አባላቱ በጉብኝታቸው ወቅት ተናግረዋል።
ሙዚየሙ ለአዲስ አበባ ከተማም ተጨማሪ ውበት የሚፈጥር መሆኑን የኢዜማ ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ አባላት መግለጻቸውን የከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ አመልክቷል።