ቀጥታ፡

ለህዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅ የሚደረጉ ድጋፎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ - የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ

አዲስ አበባ፤ ጥር 2/2016(ኢዜአ)፦ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ድጋፎች ሁሉ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ምክትል ፕሬዝዳንት ወይዘሮ መስከረም አበበ ገለጹ።

የሊጉ ስራ አስፈፃሚ አባላት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጎብኝተዋል።


 

በጉብኝቱ ላይ ወይዘሮ መስከረም አበበ እንደገለጹት ሴቶች የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ እገዛ አድርገዋል።

የብሔራዊነት ትርክት መገለጫ ሁነኛ ምሳሌ የሆነው ግድብ እስከሚጠናቀቅ ድረስም ሁሉም ዓይነት ድጋፎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

እንደ ሴቶች ሊግ ጽሕፈት ቤትም በቀጣይ ሰፋፊ ስራዎችን ለመስራት እቅድ እንደተያዘ እና ሴቶችም በሚካሄዱ ንቅናቄዎች ላይ እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ አሻራቸውን እያሳረፉ እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ሊጉ ለህዳሴ ግድብ ከክረምት ወራት ጀምሮ ከፍተኛ ንቅናቄ በማካሄድ ከ127 ሚሊዮን ብር በላይ የቦንድ ግዢ ለመፈፀም ያስቻለ ተግባር ማከናወኑም ተገልጿል።

የሊጉ ስራ አስፈጻሚ አባላት የህዳሴ ግድብን የጎበኙት በአሶሳ ከተማ እየተካሄደ ከሚገኘው የግማሽ አመት የስራ አፈፃፀም መድረክ ጎን ለጎን ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም