ቀጥታ፡

ቋሚ ኮሚቴው የኢትዮጵያ ባህር ኃይልን ጠቅላይ መምሪያ ጎበኘ

አዲስ አበባ፤ ጥር 01 /2016(ኢዜአ)፦ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት የኢትዮጵያ ባህር ኃይልን ጠቅላይ መምሪያ ጎበኙ።

የኢፌዴሪ ባህር ኃይል ምክትል አዛዥ ሬር አድሚራል ናስር አባ ዲጋ እና የመስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች ለቋሚ ኮሚቴው አባላት አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የኢፌዴሪ ባህር ኃይል ምክትል አዛዥ ሬር አድሚራል ናስር አባ ዲጋ በዚሁ ወቅት እንዳሉት የኢትዮጵያ ባህር ኃይል ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ በዘመናዊ መልክ ተቋቁሟል።

በአሁን ወቅትም  በሰው ኃይል አቅም እና በመሰረተ ልማት ግንባታ እራሱን  በማደራጀት ስኬታማ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ቋሚ ኮሚቴው በመስክ ምልከታው የባህር ኃይሉ ህዝብና መንግስት የጣሉበትን አደራ በቁርጠኝነት ለመወጣት እየሰራ ባለው ስራ ላይ ውይይት እንደሚያካሂድ ተገልጿል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም