ቀጥታ፡

መንግሥት ጠንካራ የሎጅስቲክስ ሥርዓት ለመገንባት በትኩረት እየሰራ ነው

አዲስ አበባ፤ታህሳስ 30/2016(ኢዜአ)፦ መንግሥት ጠንካራ  ሎጂስቲክስ    ለመገንባት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ ደንጌ ቦሩ ተናገሩ። 

በኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን አዘጋጅነት በኢትዮጵያ የሎጀስቲክስ ዘርፍ መሪ እቅድ ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው። 

በመድረኩ ዲፒ ግሎባል በተሰኘ አማካሪ ድርጅት የተጠና የሎጅስቲክስ መሪ እቅድ ቀርቦ ውይይት እየተካሄደበት ነው። 

የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ ደንጌ ቦሩ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት፤ ሎጅስቲክስ ለአገር ኢኮኖሚ ቁልፍ ጉዳይ በመሆኑ የዘርፉ እቅድ በየጊዜው  ማሻሻል ያስፈልጋል። 

ሎጀስቲክስን በቴክኖሎጂ ማዘመን፣ ግልፅ አሰራር መዘርጋት ና መምራት እንደሚገባ ጠቁመው መንግሥት  ዘርፉን በጠንካራ ስትራቴጂ  ለመምራት   እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። 


 

በዛሬው ዕለት ለውይይት የቀረበው መሪ እቅድ የኢትዮጵያ ሎጅስቲክስ ዘርፍ ክፍተቶችን መለየትና የቀጣይ መዳረሻ ለመተለም አይነተኛ ሚና እንዳለው ጠቁመዋል። 

በመጀመሪያው ምዕራፍ ጥናት ተልዕኮዎችን ለመለየት፣ በዘርፉ ታላላቅ ፕሮጀክቶችን ለመተግበርና  ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ የጋራ አረዳድ ለመያዝ እንደሚያግዝ ገልፀዋል።

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም