ቀጥታ፡

ለበዓላት በሚከናወን እርድ ለቆዳና ሌጦ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል

 አዲስ አበባ ፤ታህሳስ 26/2016 (ኢዜአ)፦ ለበዓላት እርድ ሲከናወን ለቆዳና ሌጦ ጥራት ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ የኢትዮጵያ አምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ገለጸ።

በኢንስቲትዩቱ የቆዳና ቆዳ ውጤቶች ምርምርና ልማት ዴስክ ኃላፊ በለጠ ጸጋዬ፤ የበዓላት ወቅት በርካታ ቆዳ የሚሰበሰቡበት መሆኑን ገልጸዋል።

ይህም ፋብሪካዎች በከፍተኛ ሁኔታ ቆዳ የሚያገኙበት መሆኑን ገልጸው ክምችቱ ብዛትም ስላለው ከፍተኛ ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት ነው ያመላከቱት። 

በቆዳ ላይ ከእርድ በፊትም የተለያዩ ችግሮች እንዳሉ ገልጸው በእርድ ወቅትም በቸልተኝነት በቆዳው ላይ የሚፈጠሩ ቀዳዳዎች ቆዳውን ከጥቅም ውጭ እያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።

በበሬ ቆዳ ላይ በቅርጫ ወቅት አጥንት የመከስከስ ሁኔታ ቆዳን እየጎዳ መሆኑንም አመላክተዋል። 

የቆዳና ሌጦ ውጤቶች በሥራ ዕድል ፈጠራና የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት ጭምር ትልቅ አስተዋጽዖ ያለው መሆኑን ጠቁመው ይህንን ኃብት በአግባቡ መጠበቅ ይገባል ብለዋል። 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም