ቀጥታ፡

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በወቅታዊ የፀጥታ ጉዳዮች ላይ እየመከረ ነው

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 24/2016(ኢዜአ)፦ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በወቅታዊ የክልሉ የፀጥታ ጉዳዮች ላይ በሆሳዕና ከተማ እየመከረ ነው።

በመድረኩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሳውን ጨምሮ በክልሉ የሚገኙ የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊዎችና የፖሊስ ኮሚሽነሮች ተገኝተዋል፡፡


 

ምክክሩ በዋናነት በክልሉ አጠቃላይ የፀጥታ አሁናዊ ሁኔታ፣ ባጋጠሙ ችግሮችና በተወሰዱ መፍትሄዎች ላይ ያተኮረ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

ከዚህ ባለፈም በክልሉ አዳዲስ የፀጥታ ስጋቶች ካሉ መለየት እና መፍትሄ ማስቀመጥ ላይ እንደሚያተኩር ተገልጿል።

በሌላ በኩል ወቅቱ የገና በዓል የሚከበርበት በመሆኑ ጸጥታ ለማስከበር እየተሰሩ ያሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ላይ እንደሚመክር ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም