ለበዓል የሚፈለጉ ምርቶች እጥረት እንዳያጋጥም እየተሰራ ነው - ኢዜአ አማርኛ
ለበዓል የሚፈለጉ ምርቶች እጥረት እንዳያጋጥም እየተሰራ ነው
አዲስ አበባ፤ታህሳስ 24/2016(ኢዜአ)፦ ለበዓል የሚፈለጉ ምርቶች እጥረት እንዳያጋጥም እየተሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ ገለጹ።
በአዲስ አበባ ከተማ በምክትል ከንቲባ ጃንጥራር አባይ የሚመራው የንግድ ቁጥጥርና የገበያ ማረጋጋት ግብረ ኃይል የግብይት ስርዓቱ ያለበትን ሁኔታ በመገምገም የቀጣይ አቅጣጫ አስቀምጧል።
አቶ ጃንጥራር በግምገማው ወቅት እንዳሉት ምርት የሚያቀርቡ ድርጅቶችን እና ቦታዎችን በመለየት የትስስር ሥራ ተጀምሯል።
ለበዓል የሚያስፈልጉ ግብዓቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ለነዋሪው ቅርብ በሆኑ የቅዳሜ ገበያዎች በኢግዚቪሽንና ባዛር እንዲቀርቡ እየተደረገ መሆኑን ምክትል ከንቲባው ማስታወቃቸው ከከንቲባ ጽህፈትቤት የተገኘው መረጃ አመልክቷል።