"የአፍሪካ ቀንድ ጂኦ ፖለቲካና የኢትዮጵያ የባህር በር አማራጮች" በሚል ርእስ የተዘጋጀ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
"የአፍሪካ ቀንድ ጂኦ ፖለቲካና የኢትዮጵያ የባህር በር አማራጮች" በሚል ርእስ የተዘጋጀ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው
ሀዋሳ፤ ታህሳስ 23/2016 (ኢዜአ)÷ "የአፍሪካ ቀንድ ጂኦ ፖለቲካና የኢትዮጵያ የባህር በር አማራጮች" በሚል ርእስ የተዘጋጀ የፓናል ውይይት በሐዋሳ ዪኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው።
በዩኒቨርስቲው አዘጋጅነት በሚካሄደው በዚሁ ውይይት ላይ በዪኒቨርሲቲው አራት ምሁራን የተዘጋጁ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግበት ተጠቁሟል።
በመድረኩም ''የኢትዮጵያ የባህር በር ታሪካዊ ዳራ ምን እንደሚመስል፣ በምስራቅ አፍሪካ ጂኦ ፖለቲካና የኢትዮጵያ ሚና፣ እድሎችና ፈተናዎች፣ የኢትዮጵያ የባህር በር ዲፕሎማሲያዊና ህጋዊ አማራጮች ምንድናቸው'' በሚሉት ጉዳዮች ላይ የፓናል ውይይት እንደሚካሄድ በመድረኩ ላይ ተገልጿል።
ለአንድ ቀን በተሰናዳው በዚሁ መድረክ ላይ ዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር አያኖ በራሶን ጨምሮ ምክትል ፕሬዝዳንቶች፣ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብና ምሁራን እየተሳተፉ ይገኛሉ።