ቀጥታ፡

በአዲስ አበባ ተቋርጦ የነበረው በአሽከርካሪዎች ላይ የሚደረገውን የአልኮል ቁጥጥር ሐሙስ ይጀመራል

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 22/2016(ኢዜአ)፦  በአዲስ አበባ ተቋርጦ የነበረው በአሽከርካሪዎች ላይ በትንፋሽ የሚደረገው የአልኮል ቁጥጥር ከመጪው ሐሙስ ጀምሮ ዳግም ይጀምራል። 

ለዚህም የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለሥልጣን 8 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ወጪ ያደረገባቸውን 75 የአሽከርካሪዎች የአልኮል መቆጣጠሪያ መሣሪያዎችን ለትራፊክ ፖሊስ አስረክቧል።


 

መሣሪያዎቹን የባለሥልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አማረ ታረቀኝ በአዲስ አበባ ፖሊስ ለትራፊክ ቁጥጥር መምሪያ ምክትል ዳይሬክተር ኮማንደር ሙሉጌታ ቢተው ዛሬ አስረክበዋል።

በአዲስ አበባ ሲካሄድ የነበረው የአሽከርካሪዎች የአልኮል ቁጥጥር በኮቪድ 19 ወረርሺኝ የተቋረጠ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን አሁን ላይ ምቹ ሁኔታዎች በመኖራቸው ታህሳስ 25/2016 ዓ.ም ይጀመራል ተብሏል። 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም