ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የቅድመ ክፍያ ቆጣሪ ደንበኞቹን በበዓላትና እረፍት ቀናትም እንደሚያስተናግድ ገለጸ

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 22/2016(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የቅድመ ክፍያ ቆጣሪ ደንበኞቹን በበዓላትና እረፍት ቀናትም በተለያዩ ማዕከላት እንደሚያስተናግድ አስታውቋል።

አገልግሎቱ በበዓላት እና በዕረፍት ቀናት ያለውን የካርድ መሙላት አገልግሎት ለደንበኞቹ ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ የሚሰራው በአዲስ አበባ ከተማ ስር ባሉ የደንበኞች አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ነው።

በዚህ መሰረትም ዘወትር ከሰኞ እስከ ዕሁድ ከጠዋቱ 2 ሰዓት እስከ ቀኑ 11 ሰዓት በተወሰኑ የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት የቅድመ ክፍያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝም ገልጿል።

ስለሆነም ደንበኞቻችን የኃይል መሙላት አገልግሎቱን ከሰኞ እስከ ዕሁድ ከታች በተገለፁት ማዕከላት የሚያገኙ መሆኑን አገልግሎቱ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባስተላለፈው መልዕክት አስታውቋል።


 

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም